የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: ጩኸት እና ንግግር: በታክሲ እየሄድኩ ነው፡፡ መካከለኛው ወንበር ነው የተቀመጥኩት፡፡ አንዲት ሴትዮ በስልክ በንዴትያወራሉ፡፡ በጩኸታቸው መጨረሻ «እንዲያውም ካሁን በኋላ ካንተ ጋር መኖር አልችልም፤ በቃ»ብለው ዘጉት፡፡ በታክሲ ውስጥ የነበርነው ሁሉ በድንጋጤ እያየን ነበር ያዳመጥናቸው፡፡
ወዲያው አንዱ ቀልደኛ «እናቴ ይህንን በቃ የሚል ቃል እንኳን ቢተውት፤ ሌላ ትርጉም ያመጣል»ሲል ሁላችንም ከድንጋጤው ወጥተን ሳቅን፡፡ስልኩን ሲጨርሱ ሁላችንም ወደርሳቸው መዞራችንን ሲያዩ ደንገጥ አሉ፡፡ አጠገባቸው ተቀምጠውየነበሩት አዛውንትም ፈገግ አሉላቸው፡፡«ልጄ ልበልሽ ወይስ እናቴ?» አሉ አዛውንቱ በነጭ ሪዛቸው ውስጥ ፈገግታቸውን እያሳዩ፡፡«ኧረ ልጄ ይበሉኝ» አሉ ተናደው የነበሩት ሴትዮ«በጣም ጥሩ» አሉና አዛውንቱ ከወንበራቸው ላይ ተመቻቹ፡፡«እይውልሽ በጣም ስትናደጅ እና በጣም ስትደሰች እባክሽ ውሳኔ አትወስኝ» አሏቸው፡፡ የሁላችንምጆሮ ወደ አዛውንቱ አቀና፡፡«ቅድም እየተናገርሽ አልነበረምኮ፣ እየጮኽሽ ነበር፡፡ ጩኸት እና ንግግር ይለያያሉ፡፡ መናገርተረጋግቶ፣ አስቦ፣ ውጤቱን አስልቶ ነው፡፡ መጮኽ ግን አፍ እንዳመጣ ነው፡፡» አሏቸው፡፡«አሁን ምን እንደተናገርሽ ብጠይቅሽ አታስታውሽውም፤ ምክንያቱም አንደበትሽ ሳይሆን ምላስሽ ብቻነበራ የሚናገረው»«በአንደበት እና በምላስ መካከል ልዩነት አለ እንዴ» አለች አንዲት ወጣት፡፡ሌሎችም ራሳቸውንነቀነቁ፡፡«ምላስ እና አንደበትማ ይለያያል፡፡ ምላስ ማለት ይቺ ቅልብልቢቱ ናት፡፡» አሉና ምላሳቸውንአውጥተው አቅለበለቧት፡፡ ሁላችንም ሳቅን፡፡ ሾፌሩ በተለይ ከልቡ ሲስቅ ጊዜ፡፡ «ሾፌር ይኼጨዋታ አንተን አይመለከትም ዝም ብለህ ንዳ» አሉት፡፡«ይቺ እንዳ መጣላት የምትለፈልፈው...