አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በ1996 ዓ.ም. የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 436(ሐ)ን በመተላለፍ ፈጽሟል የተባለውን በሕገወጥ መንገድ መብትን የማስከበር ወንጀል፣ ለግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ቀርቦ እንዲያስረዳ በተላለፈለት ጥሪ መሠረት ባለመቅረቡ ታስሮ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተላለፈ፡፡ ትዕዛዙን ያስተላለፈው የፌዴራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የየካ ምድብ ወንጀል ችሎት ሲሆን፣ ኃይሌ ታስሮ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ያስተላለፈው የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ሚያዝያ 18 ቀን 2004 ዓ.ም. ላቀረበው የወንጀል ክስ ግንቦት 10 ቀን 2004 ዓ.ም. መልስ ይዞ እንዲቀርብ በተላለፈለት ጥሪ መሠረት ፍርድ ቤት ሳይቀርብ በመቅረቱ ነው፡፡
አትሌት ኃይሌን ለክስ ያበቃው ክስተት ህዳር 24 ቀን 2004 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት አካባቢ በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11/12 ክልል ልዩ ቦታው ሃያ ሁለት እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ በተፈጸመ ድርጊት ነው፡፡
በተጠቀሰው አካባቢ በሚገኘው የአትሌት ኃይሌ ሕንፃ ውስጥ ተከራይተው ከሚሠሩትና ተበዳይ ከሆኑት አቶ አዲስ ደገፋ ጋር በኪራይ ውል ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት ጉዳዩ ፍርድ ቤት ደርሶ በክርክር ላይ እንደነበር ክሱ ያስረዳል፡፡ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ውሳኔ ሳያገኝ አቶ አዲስ ይሠሩበት የነበረውን ቢሮ ቁልፍ በሌላ ቁልፍ በመቀየር እንዳይገለገሉበት ማድረጉን ክሱ ያብራራል፡፡ ድርጊቱም በሕገወጥ መንገድ መብትን ማስከበር ወንጀል መሆኑን ጠቅሷል፡፡
አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የፍርድ ቤቱን ጥሪ አክብሮ ፍርድ ቤት ባለመገኘቱ በ48 ሰዓታት ውስጥ ታስሮ ለግንቦት 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡